የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ
የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ አሳልፏል።
በዛሬው ዕለት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተካሄደው 45ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የአለም ቅርስ ጉባኤ ላይ የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርስነት የተመዘገበው በኢትዮጰያ ኹለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን፤ በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።
45ኛው የአለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ኹለት ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻዎችን በአለም ቅርስነት ማስመዝገቧን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ በተመሳሳይ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በደቡብ ኢትዮጵያ ጌዴኦ ዞን የሚገኘው የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja