በአዳማ ስጋ በሚቆርጥበት ቢላ የሬስቶራንቱን ስራ አስኪያጅ በስለት ወግቶ የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!
በአዳማ ከተማ ደምበላ ክፍለከተማ የአንድ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ በስለት ተወግታ መገደሏን ተከትሎ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ፖሊስ በተከራየበት ሆቴል ውስጥ በወለጪቲ ከተማ መያዙን አስታውቋል።
በአዳማ ከተማ አስተዳደር ደምበላ ክፍለከተማ ወንጂ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ የአንድ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ የሆነችውን የ24 ዓመት ወጣት ተጠርጣሪዉ በስለት ወግቶ መሰወሩን እና በፖሊስ ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪውን መያዙን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ተጠርጣሪው የእቴቴ ባርና ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ የሆነችውን ሃሴት ደርቤ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በሬስቶራንት ውስጥ የስጋ ቆራጭ ሆኖ እየሰራ ባለበት በስራ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስጋ በሚቆርጥበት ቢላዋ ወደ የግል ተበዳይን ወግቶ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ ተገልጿል።
ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብ እና ተጎጂዋ በስራ ምክንያት በተደጋጋሚ ይጋጩ እንደነበር ተጠቁሟል።ፖሊስ ድርጊቱን ከፈጸመ እለት ጀምሮ ክትትል እና ምርምር እያደረገ እንደነበረ እና በሂደቱ እገዛ ላደረጉ አካላት በሙሉ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ምስጋና ማቅረባቸውን ብስራት ራዲዮ ዘግቧል።(ብስራት-ራዲዮ)
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ