ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ ተመረቀ!
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የእድሳት ሥራ ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ታቦተ ሕጉ ወደ መቅደሱ ገብቷል።
ላለፉት 3 ዓመታት በእድሳት ላይ የቆየው ካቴድራሉ ከተመሰረተ 81 ዓመታትን ማስቆጠሩ ተገልጿል።
ታቦተ ሕጉ ጥንታዊነቱን ጠብቆ ወደ ታደሰው ካቴድራል በዛሬው እለት የገባ ሲሆን በነገው ዕለት በደማቅ ስነ-ስርአት ቅድስት ሥላሴ የንግስ ስርአት ይፈፀማል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የቤተክርስቲያኒቱ የኃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ