የኦሮሚያ ክልል መንግስት በህዳር ወር ከመንግስት ጋር የሰለም ስምምነት ለተፈራረሙ ሶስት የቀድሞ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ሹመት መስጠቱን አስታወቀ፡፡
በዚህ መሰረትም የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን አዛዥ የነበሩት ያደሳ ነጋሳ (በትግል ስሙ ጃል ሰኚ) በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ተደርገው ተሾመዋል።
በተጨማሪም አቶ ኦሮሚያ ረቡማ የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ ምክትል ሃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን አቶ ቶሌራ ረጋሳ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ከነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል ትላንት ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል።
የኦሮምያ ክልል መንግስት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል የሰላም ስምምነት ፈርመዋል ሲል በወቅቱ ገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ