ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት እንደተፈጸመበት አገልግሎቱ አስታወቀ
በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሰባት ወራት 50 ሚሊየን 222 ሺህ 987 ነጥብ 7 ብር የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት እንደተፈጸመበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ በ22 የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ላይ ርምጃ መውሰዱንም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የተፈፀመው ስርቆትና ውድመትም የኃይል ስርቆት፣ የትራንስፎርመር ስርቆት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ጉዳት፣ የመሰረተ ልማት ስርቆት፣ የተቋሙ ሠራተኞችን ሥራ እንዳይሠሩ ማወክና የኬብል ስርቆትን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጿል።
በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ 163 የኃይልና መሰረተ-ልማት ስርቆት ወንጀል መፈጸሙን የገለጸው ተቋሙ ከእነዚህ መካከል 11 የወንጀል ጉዳዮች ውሳኔ ማግኘታቸውን አስታወቋል። በዚህም 13 ተከሳሾች ከሁለት ወር ቀላል እስራት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን አክሎ ገልጿል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ከ #መተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ ድረስ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር በአስር ቀናት ውስጥ መዘረፉን ተቋሙ ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እያለ ከደንበኞች የቀረቡ የብልሹ አሠራርና ሙስና ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ በ22 አመራርና ሠራተኞች ላይ አሥተዳደራዊ ርምጃ መውሰዱንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመግለጫው አስታወቋል፡፡ በዚሁ መሠረት አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎ ሦስቱ በጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እና 19ኙ ደግሞ በደመወዝ ቅጣት መቀጣታቸውን ነው ያስታወቀው፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ