አሳዛኝ ዜና🕯🕯
ተወዳጁ ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት አረፈ!
አመለ ሸጋው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
ህልፈተ ሕይወቱ ያጋጠመው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።
ድምፃዊው በስፍራው የተገኘው ቢጂአይ ወልቂጤ ብራንች የሠራተኞች ቀንን ሲያከብር ለተዘጋጀው መርሐ ግብር እንደነበር ተገልጿል።
#ድምፃዊው በዝግጅቱ ስፍራ መድረክ ላይ እንደወጣ ገና ከመጀመሩ ይቅርታ ብሎ የወረደ ሲሆን፣ በኋላም «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ተገልጿል።
ከቦታው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወልቂጤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲወሰድ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል።
በዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ሰፊ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፤ «አሁን ገባኝ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ»፣ «ናተይ» እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ በተጫወቱት «ጉዳዬ» በተሰኙት ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል።
በተጨማሪም «10 ከ 10 ይገባሻል» እና «ሰላም አላት» የተሰኙ አልበሞችን እንዲሁም በቅርቡ «እንዳማረ» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሶ ነበር።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለሙዚቃ አፍቃሪያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja