ተስማሙ‼️
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሶማሊያው መሪ ጋር ከስምምነት ደረሱ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ፣ በባሕር በር ውዝግብ ሳቢያ በአገሮቻቸው መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቁርሾ ለመፍታት ትናንት ምሽት በፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ኹለቱ አገራት አንዳቸው የሌላኛቸውን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማክበር፣ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የንግድ ማዕቀፎችን ለመፍጠር እና በአንዲት ሱማሊያ ማዕቀፍ ሥር ለኢትዮጵያ ዘላቂ የኾነ የባሕር በር ለማስገኘት ተስማምተዋል።
ዐቢይና ሞሐመድ፣ በኹለቱ አገሮች መካከል በባሕር በር ውዝግብ ዙሪያ ውጥረት ከተፈጠረ ወዲህ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አቀራራቢነት ለመጀመሪያ ጊዜ እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል። መሪዎቹ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአንካራ ስምምነት' ዝርዝሩ ምን ይሆን?
"በሶማልያ መንግስት ባለመብትነት ስር በሚከናወን የንግድ ውል፣ ሊዝ እና ሌላ አሰራር ሁለቱም ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ይከናወናል፣ ይህም ኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር የመጠቀም እድል ይኖራታል።
ይህን ጉዳይ ለማስፈፀም ከመጋቢት 2017 ዓ/ም በፊት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሙ የማመቻቸት ስራ ይሰራል፣ በአራት ወር ውስጥ ደግሞ ስምምነት ይፈረማል።"
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን መሀመድ በመግለጫው ሀገራቸው የኢትዮጵያን የባህር በር የኪራይ ፍላጎት እንደሚረዱና ለዚህም ለመተባበር ፈቃደኛ ነን ብለዋል።
መሀመድ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት ሀገራቸው ዕውቅና እንደምትሰጥ አውስተው ምስጋናም አቅርበዋል።
https://t.me/ethio_mereja_news