#ከ5530 ዘመን በኋላ የተደመሰሰው የዕዳ ደብዳቤ
ዮርዳኖስ ቃሉ ያርዴን ከሚለዉ የእብራይስጥ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም “ወራዲ፣ የሚወርድ፣ ወራጅ ወንዝ” ማለት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን 175 እንዲሁም በሐዲስ ኪዳን 15 ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ስሙ የተጠቀሰ ቅዱስ ስፍራ ነዉ፡፡ ዮርዳኖስ ወንዝ ከሶርያ ምድር፣ ከሄርሞን ወይም በግእዙ አርሞንኤም፣ በአማርኛዉ ጎላን ከሚባለው (እስራኤል በኃይል የተቆጣጠረችው ንብረትነቱ ግን የሶሪያ የሆነ) ተራራ ሰሜናዊ ክፍል ተነስቶ ወደ ደቡብ የሚፈስ ነው፡፡ ሶርያን፣ ጆርዳን ወይም ዮርዳኖስ የምትባለውን ሀገር፣ የፍልስጤም አስተዳደርና እስራኤልን በማዋሰን በአማካይ ከ314 እስከ 320 ኪ.ሜ ተጉዞ ሙት ባህርን የሚቀላቀል የእስራኤል ትልቁ ወንዝ ነው፡፡
ይህ ወንዝ አዳኝና ፈዋሽም ነዉ የሶርያዉ ሰዉ ንዕማን በለምጽ ሲሰቃይ ነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ እንዲፈውሰው ወደ እስራኤል መጣ፡፡ ነቢዩም በዮርዳኖስ ወንዝ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እንዲል ነግሮት፣ መጀመሪያ ቢያንገራግርም ኋላ ግን ይህን ሲፈጽም ከለምጹ ድኗል፡፡ ጻድቁ ኢዮብ በደዌ ሥጋ ሲሰቃይ በዚሁ ወንዝ ታጥቦ ነበረ ቁስሉ የነጻው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ኤሊያስም በእሳት ሰረገላና ወደ ሰማይ ሲነጠቅ ደቀ መዝሙሩ ነቢዩ ኤልሳዕ በሁለት አጥፍ የኤልያስን መንፈስ የተቀበለው በዮርዳኖስ ወንዝ ነዉ /2ኛ ነገ 2፡1-15/፡፡ ከመነሻው በአንድ ምንጭ የሚፈልቀው ዮርዳኖስ በሁለት ተከፍሎ “ዮር” እና “ዳኖስ” ሆኖ ሲፈስ ይቆይና ከታች መልሶ ይገናኛል፡፡ ዮርዳኖስ የሚለው ስሙም መነሻው ይህ ነው፡፡
በዘመነ ብሉይ በነቢዩ ኢሳይያስ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንሰሓ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ እንደሚመጣ የተነገረለት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙርያ ያሉ ሕዝቦችን “መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ” እያለ ኃጢያታቸዉን እየተናዘዙ የንሰሃ ጥምቀት ያጠምቅበት የነበረው የዮርዳኖስ ወንዝ ከኢያሪኮ በስተምሰራቅ በኩል ይገኛል፡፡ ማቴ 3፡1-6 ሁለቱም በሚገናኙበት ስፍራ የትህትና ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ ምድር ፈጣሪ ሲሆን በሰዉ እጅ ራሱን ዝቅ አድርጎ የጽድቅ ሥራ መሥራት ይገባ ዘንድ ሊያስተምረን ተጠመቀ፡፡ ጌታችን ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ?
ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ ከገነት ከወጡ በኋላ መከራ አጸናባቸውና እንዲያቀልላቸው አዳም የዲያብሎስ ባሪያ፣ ሔዋን የዲያብሎስ ገረድ ብለው ጽፈው እንዲሰጡት ነገራቸው፡፡ እነዚህን የእዳ ደብዳቤዎች አንዱን በሲኦል ሌላኘውን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ቀብሮት ነበርና የዮርዳኖሱን በዩሐንሰ እጅ ሲጠመቅ እንደ ሰወቅነቱ ተረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አጥፍቶላቸዋል፡፡ ማቴ 3፡15—17 ቅዱስ ኤፍሬምም በሰኞ ውዳሴ ማርያም “የአዳምና የሄዋን የእዳ ደብዳቤያቸዉን ቀደደ ደመሰሰ” ይላል፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ የተጠመቀነት ምክንያት ደግሞ በቅዱስ ዳዊት “ባህር አየችህ ሸሸችም፣ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ” ተብሎ የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ራሳቸውን የለዩ፣ እንደ ዮሐንስ ያሉ ገዳማውያንን በመርዳት በዓታቸውንም በማጽናት ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444