በፍቅርና በአንድነት በመቆም ለሀገር ሰላምና እድገት የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባል - ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ሁላችንም በፍቅርና በአንድነት በመቆም ለሀገር ሰላም እና እድገት የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጹ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የጥምቀትን በዓል እያከበሩ ለሚገኙ ምዕምናን ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ የሰው ልጅ ዘላቂ ሕይወትን መቀዳጀት የሚችለው ፈሪሃ እግዚአብሄርን መላበስ ሲችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ፈጣሪ ከሰዎች የሚጠብቀውን መልካም ስብእናዎች ከመላበስ አኳያ የሚስተዋሉ ችግሮች የሰው ልጅን ለአደጋ ሲያጋልጡ ማስተዋል እየተለመደ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ሁሉም ቆም ብሎ ስለሰላም ማሰብ ይኖርበታል ብለዋል።
ሁሉም በፍቅርና በአብሮነት በመቆም ለሀገር ሰላም እና እድገት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት መወጣት እንዳለበት ነው የገለጹት።
ህብረተሰቡ ፈጣሪ የሰጠውን ጸጋ በመጠቀም እርስ በእርስ በመተሳሰብና በአብሮነት ለሀገር ሰላም እና እድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን መቅረፍ ይኖርበታልም ብለዋል።
ኢዜአ