ተማሪዎች ሰለስራ ቅጥርና ፈጠራ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እየተሠራ ነው።
------------------------------------------
(የካቲት 22/2017 ዓ.ም) በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር እና በኢንፎ ማይንድ ሶሊሽን መካከል የተፈረመውን የትብብር መግባቢያ ስምምነት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናውኗል።
የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በትብብሩ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ሚንስትር ዴኤታው በማያያዝም ዜጎች በሀገሪቱ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ከራሳቸው ባለፈ ለሀገራቸው አበርክቶ እንዲኖራቸው የትምህርት ዘርፉና ተባባሪ አካላት ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሜጄና በበኩላቸው የትብብር ፕሮግራሙ ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸውም ይሁን ወደ ስራው አለም ሲቀላቀሉ የሚያስፈልጓቸውን ክህሎቶች እንዲገነቡ የሚያግዝ በመሆኑ የትምህርት ዘርፉ አስፈላጊውን ጥረትና ድጋፍ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።
በዚህም በቀጣይ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ቅጥርና ፈጠራ ማጎልበቻ ማዕከላት እንደሚገነቡ ገልጸዋል።
የኢንፎ ማይንድ ሶሊሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ የሱፍ ረጃ በበይነ መረብ ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን በስራ ቅጥርና ፈጠራ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዬች ላይ ያላቸውን አቅም ለማጎልበት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ተቋማቸው ሚናውን እንደሚወጣ አብራርተዋል።
የትብብር መርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የሀገሪቱን የስራና ቅጥርና ፈጠራ ነባራዊ ሁኔታ የተመለከቱ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።