Bright Minds Academy☀️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


In our channel :
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info and news
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇


I strongly ____ you to lose weight.
Poll
  •   advice
  •   advise
4 votes


She is expected ___ the job.
Poll
  •   getting
  •   to get
4 votes


Bag of bones
Poll
  •   ቀጭን
  •   ወፍራም
10 votes


Dog's age
Poll
  •   ረዥም ጊዜ
  •   አጭር ጊዜ
10 votes


A: I enjoyed the game. B: ________
Poll
  •   So do I.
  •   I'm also.
  •   So did I.
  •   So am I.
10 votes


የታገተ ሰው ለማስለቀቅ የሚከፈል ገንዘብ
Poll
  •   Fine
  •   Ransom
  •   Tax
  •   Alimony
9 votes


He spent three years BEHIND BARS.
Poll
  •   ውጪ ሀገር
  •   በ እስር ቤት
  •   በ ሆስፒታል
  •   በ ዩኒቨርሲቲ
9 votes


I will pay ___ advance. ቅድሚያ እከፍላለሁ።
Poll
  •   at
  •   in
  •   for
  •   on
25 votes


She did it ___ purpose. ሆን ብላ ነው ያደረገችው።
Poll
  •   on
  •   in
  •   at
  •   by
23 votes


🤩እንኳን ለ ኢድ አል አድሃ (አረፋ ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🤩

🤩 🤩 ለእስልምና ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ ብያለሁ🤩🤩


⭐ መልካም በዓል


#RemedialExam

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡

በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡

ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡


✳️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! 😊

🔰 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል።  ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ።  ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ: 
•📌 አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።

•📌 በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ። 

•📌 የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።

📌• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።  ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

🙌🏾 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤

🎯• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። 

🎯• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።

🎯 • ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።   ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። 

🎯• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። 

🎯• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

🔰 ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

🍁 • ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።  

🍁• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 

🍁• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

🍁 • በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር። 

🍁• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

🍁  • በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

🍁• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 

🍁• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት። 


ምንም ሳትጠብቅ ወደደችኝ 
ያለ እረፍት ለዘጠኝ ወር ሸሸገችኝ
ድካምና ህመም ሳያግዷት ወለደችኝ
ለሁለት አመት በጀርባዋ አኖረችኝ
እየራባት ለኔ ጡቷን አጠባችኝ
እሷ ቀልጣ ለህይወቴ ሻማ ሆነችኝ
ከፊት ሆና የፍቅርን ጥግ አሳየቺኝ
ሆዷን አስራ ለኔ ምርጡን መገበቺኝ
እያመማት ለኔ ጤናን አደለችኝ

መች ልመልስ የውለታዋን ቅንጣት
ዘላለሜን ብኖር እንኳ ስጦራት
ከየት አምጥቼ የሷን ያህል ጥንካሬ
ምጠግናት ልክ እንደሷ ተሰብሬ
አድጌ እንኳ ከጎኔ ናት ሁሌ አትጠፋም
እሷ እስካለች ለአንድም ሰከንድ አልከፋም

ማን መርምሮ ይድረስበት
ያንቺን ፍቅር የእናትነት
ማንስ ያጥናው ይመርምረው
ከማን ይሆን የእናት ፍቅር ለእናቶች የተቸረው?

መልካም የእናቶች ቀን!! ❤️


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
መልካም የእናቶች ቀን ❤️


📫𝖉𝖊𝖆𝖗 𝖒𝖔𝖒...
🎁🐚🐚🐚🐚✅ 🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
                 💐 🔠🅰️🔠 💐

❤️ዛሬ የእናቶች ቀን ነው🤱

📼እስቲ እናታቹን በአጭር ቃል ግለፁልን❤️
🧠


ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።


#DV2026

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2026 አሸናፊዎች ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራትን ሁሉ የሚጠቃልል ሲሆን #ኢትዮጵያም አንዷ ናት።

የዲቪ ሎተሪ መውጫ መድረሱን ተከትሎ " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች ሊጠነቀቁ ይገባል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2026 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ ብቻ ነው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።


ዘጠነኛ ክፍል mathematics ምን ያክል አንብባችኋል።

1. Which of the following best describes the notion of sets?
A) A collection of unrelated elements
B) A group of elements with a common property
C) A single element
D) A random assortment of numbers

2. What is the result of the operation of intersection between two sets?
A) Elements that are common to both sets
B) All elements of the two sets combined
C) Elements unique to the first set
D) Elements unique to the second set

3. Which of the following is an example of a rational number?
A) √2
B) -5
C) 3/4
D) π

4. What type of number is √2?
A) Rational
B) Integer
C) Irrational
D) Real

5. What is the sum of the interior angles of a convex polygon with 5 sides?
A) 540 degrees
B) 360 degrees
C) 720 degrees
D) 180 degrees

6. What is the ratio of perimeters of two similar plane figures if the ratio of their sides is 3:5?
A) 3:5
B) 5:3
C) 8:15
D) 15:8

7. In solving equations, what is the value of x in the equation 2x + 5 = 15?
A) x = 5
B) x = 6
C) x = 7
D) x = 8

8. Which of the following is an example of a linear inequality?
A) x² > 5
B) 3x + 4 < 10
C) √x ≥ 3
D) |x| = 2

9. What trigonometric ratio represents the ratio of the opposite side to the hypotenuse in a right-angled triangle?
A) Sin
B) Cos
C) Tan
D) Cot

10. What is the sum of the exterior angles of a convex polygon with 7 sides?
A) 540 degrees
B) 360 degrees
C) 720 degrees
D) 180 degrees

11. Which of the following is a scalar quantity?
A) Velocity
B) Force
C) Mass
D) Displacement

12. What is the representation of a vector with magnitude 5 and direction due east?
A) 5i
B) 5j
C) 5i + 5j
D) 5i - 5j

13. How many degrees are in a full rotation in a two-dimensional vector space?
A) 180 degrees
B) 360 degrees
C) 90 degrees
D) 270 degrees

14. Which of the following is an example of a rational number?
A) √3
B) 2/3
C) -√5
D) π

15. What is the result of the operation of union between two sets?
A) Elements that are common to both sets
B) All elements of the two sets combined
C) Elements unique to the first set
D) Elements unique to the second set

16. What type of number is 5/7?
A) Rational
B) Integer
C) Irrational
D) Real

17. What trigonometric ratio represents the ratio of the adjacent side to the hypotenuse in a right-angled triangle?
A) Sin
B) Cos
C) Tan
D) Cot

18. What trigonometric ratio represents the ratio of the opposite side to the adjacent side in a right-angled triangle?
A) Sin
B) Cos
C) Tan
D) Cot

19. Which of the following is an example of a linear equation?
A) x² = 9
B) 2x + 3 = 7
C) |x| = 4
D) √x = 2

20. What is the result of the operation of difference between two sets?
A) Elements that are common to both sets
B) All elements of the two sets combined
C) Elements unique to the first set
D) Elements unique to the second set

Answer
1. B 
2. A 
3. C 
4. C 
5. A 
6. A 
7. B 
8. B 
9. A 
10. B 
11. C 
12. A 
13. B 
14. B 
15. B 
16. A 
17. B 
18. C 
19. B 
20. C


🎉ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን🙏🙏🙏

20 last posts shown.