ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ያዘጋጀውን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን ሪፖርት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ይፋ አደረገ።
ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጥረት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በፈጠራ በማጎልበት እና ዘላቂ ልማትን በማምጣት ረገድ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት እንዲሁም የሀገሪቱን ዲጂታል ስነ-ምህዳር ከማሳደግ አንጻር እየተደረገ ያለውን ጥረት ዳስሷል።
የጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ዘገባ እንደሚያመለክተው የቴሌኮም ዘርፍ በኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሆኖ በመቀጠል እ.ኤ.አ በ2023 በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ያበረከተው ተጨምሮ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 8% ደርሷል።
በሪፖርቱ የተዳሰሱ ግኝቶች ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እያከናወነቻቸው ለሚገኙ ተግባራት ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን የሚፈጥርላት ሲሆን በተለይም ለዜጎች አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያጎለብት ይታመናል፡፡
ኢንጅነር ባልቻ ሬባ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ እና ኢትዮ ቴሌኮም የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን ያሰባሰበውን መርሃ ግብር በማዘጋጀታቸው ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያን ቀጣይ የዲጂታል ጉዞ ለማፋጠን ጠቃሚ ግብዓት ለሚሆነው የ ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ አድናቆታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
ሪፖርቱን ያንብቡ፡ https://bit.ly/3NCN7Kx