በጆን ጂዩስቲ የዓለም አቀፉ የሞባይል ኮሙኒኬሽን ሲስተም ማህበር (ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ) ዋና የሬጉላቶሪ ኃላፊ የሚመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልኡካን በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኙ፡፡
የዓለም አቀፉ የሞባይል ኮሙኒኬሽን ሲስተም ማህበር (ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ) ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልኡክ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኙ፡፡
ልኡካኑ በማዕከሉ የሀገራችንን የቴሌኮም ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስከደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚያመላክቱ ቴክኖሎጂዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ ስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ የማዕድን ልማት እና ቱሪዝም የመሳሰሉ ሶሉሽኖች ለሀገራችን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግንባታ ስለሚኖራቸው ቁልፍ ሚና ተግባራዊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
ጎብኚዎቹ በኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ በቀረቡት የዲጂታል ሶሉሽኖች እና የኢትዮ ቴሌኮም አመራር ለዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት ላለው ከፍተኛ ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ ፈጠራን በማጎልበት እና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን በማሳደግ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በማፋጠን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ማዕከሉ ለሌሎች ኦፕሬተሮች አርአያ መሆኑን በመግለጽ ሌሎች የአህጉሪቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች ይህን ዘመናዊ የኤክስፒሪየንስ ማዕከል በመጎብኘት የላቀ የዲጂታል ሶሉሽኖች ተሞክሮ እንዲቀስሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#GSMA #Ethiotelecom #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #ITU