በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን ልዑክ በአንጋፋው ጅማ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ጋር የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ለማዘመን እና በስማርት ካምፓስ ትግበራ ዙሪያ መክረዋል።
ልዑኩ የዩኒቨርስቲውን ዳታ ሴንተር የጎበኘ ሲሆን፣ በአይሲቲና በቴክኖሎጂ ረገድ ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ስለሚገኙ ተግባራት እንዲሁም ከኩባንያችን ጋር በአጋርነት ለመስራት በሚፈልጉባቸው ጉዳዮች በዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት እና ባለሙያዎች ማብራሪያ ቀርቦላቸዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በስማርት ካምፓስ፣ በጤና፣ በግብርና እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ጨምሮ በሀገራችን የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አክለውም የዩኒቨርስቲውን የዲጂታል መሰረተ ልማቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለማዘመን፣ ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም እንዲሁም የምርምር ሥራዎችን በ (big data analytics) እና የአይኦቲ (IoT) ለማዘመን በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ተቋማዊ አቅማቸውን በማቀናጀት በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የዲጂታል ክህሎትን በማዳበር እና ኢፍትኃዊ የዲጂታል ክፍፍልን (digital divide) በማጥበብ የኢትዮጵያን ዘላቂ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በታሪካዊቷ ጅማ ከተማ እና በዩኒቨርሲቲው ለነበራቸው ፍሬያማ ቆይታ እና የሞቀ አቀባበል ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
#RealizingDigitalEthiopia #Jimma #SmartCampus #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Ethiotelecom #telebirr