ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ የፌደራል መንግስቱ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነቱን ይወጣ ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ አቀረበ!።
የትግራዩን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በሙሉእነት ባለመተግበሩ የተነሳ የትግራይ ክልል ሕዝብ የከፋ ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትላንት ማምሻውን ባሠራጨው መግለጫ አሳወቀ።
የሰላም ውሉ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ታጣቂዎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ፣ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ ሕገመንግስታዊ የትግራይ ክልል ግዛት ወደነበረበት እንዲመለስ፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የሚያስገድድ እንኳን ቢሆንም እስካሁን ተፈፃሚ ባለመሆኑ የትግራይ ክልል ሕዝብ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብሏል።
በዚሁ ምክንያት በተለይም ተፈናቃዮች ለሰው ልጅ በማይመጠን የከፋ ሁኔታ ሊኖሩ የተገደዱበት ሁኔታ አሁንም በትግራይ መቀጠሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገልጿል።በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት የተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውሉ በሙሉእነት ሊተገበር ጥረቱ እንደሚቀጥል ያስታወቀ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በተለይም የተፈናቃዮች ሰቆቃ ሊያበቃ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነቱ ይወጣ ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ለአፍሪቃ ኅብረት፣ የአሜሪካ መንግስት እና ለአውሮፓ ኅብረት ጥሪው ያስተላለፈው የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ሊተገበር ጫና እንዲፈጥሩ ጠይቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትላንት ጀምሮ በመቐለ ጎዳናዎች የተቃውሞ ድምፃቸውን እያሰሙ ያሉት ተፈናቃዮች ችግራችን የማይፈቱ የውስጥ ይሁን የውጭ አካላት እንቃወማለን ብለዋል።