የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከልና ሁለት ባለ 13 ወለል ህንጻዎችን አስመረቀ
በ1 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኮርፖሬሽኑ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከል ጥራት ያለው ብሎኬት እና የኮንክሪት ውህድ በማምረት የራሱን የኮንክሪት ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በዘርፉ ያለውን የግብዓት እጥረት ይሞላልም ተብሎ ይጠበቃል።
የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ማዕከሉ በአመት 202ሺ 752 ሜትር ኩብ የኮንክሪት ውህድና እና ባለ 20 ሴንቲ ሜትር ብሎኬት በቀን 25ሺ፣ ባለ 10 ሴንቲ ሜትር በቀን እስከ 50ሺ እንዲሁም ባለ 15 ሴንቲ ሜትር በቀን 37ሺ ብሎኬቶችን የማምረት አቅም አለው።
በ1ሺ 263 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ባለ 13 ወለል ሆኖ የተገነባው የኮከበ ጽባህ ሳይት ህንጻ ሌላው ኮርፖሬሽኑ አስገንብቶ ያስመረቀው ፕሮጀክት ሲሆን ከባለ ሁለት እስከ ባለ አራት መኝታ ቤት 60 የሚደርሱ ዘመናዊ ቤቶች ያሉት ነው።
ሌላው በ1ሺ 541 ካሬሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ከባለ 1 እስከ ባለ አምስት መኝታ ቤቶች ያሏቸው መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ሱቆችን አካቶ የተገነባው ባለ 13 ወለሉ የምስራቅ አጠቃላይ ሳይትም ኮርፖሬሽኑ ገንብቶ ያስመረቀው ፕሮጀክት ነው።