ቋሚ ኮሚቴው በህንጻ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የህንጻ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ህንፃዎች ሲሰሩ ለዲዛይኖች ጊዜ ሰጥቶ በአግባቡ በመስራት የግንባታ ጊዜን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የአዋጭነት ጥናትና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽኖዎችም በአግባቡ መታየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ምክትል ሰብሳቢው ከመድረኩ ጥሩ ግብአት መገኘቱን ገልጸው፤ አዋጁ ረጅም ጊዜ የሚያገለግል እንዲሆን ተጨማሪ አስተያየቶችን በጽሁፍ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል ። ዘርፉን ለማሳደግ የሙያ ማህበራት ተጠናክረው በጋራ መስራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
በውይይቱም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የአዋጁ ማሻሻያ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የከተሞች ስታንዳርድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ገልጸው፤ የሙያ ማህበራት በጋራ ሆነው ጠንካራ አቅም መፍጠር ቢችሉ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል ።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ መዲና አህመድ አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አዋጁ የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች የህንጻ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል
በነባሩ ህግ በአፈጻጸም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፣ የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትን፣የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ግልጽና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ተገቢ ሆኖ መገኘቱን ተናግረዋል ።
ማንኛውም ሰው አዲስ ግንባታ ለማከናወን፣ ነባር ህንፃ ለማሻሻል ፣ለማስፋፋት ወይም ለማፍረስ እንዲሁም የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ በቅድሚያ ተገቢውን የግንባታ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት እና ማንኛውም ሰው የህዝብ መገልገያ የሆኑ የተጠናቀቁ ህንፃዎች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት የህንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት ገልጸዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት አዋጁን በሚመለከት አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።
በውይይቱ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ፣ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ቲንክታ
አካላት ተገኝተዋል።
(ከመልሚ)