6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው በየዘርፉ ያሉ ችግሮችን ይፈታሉ የተባሉ ሶስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕንፃዎች ረቂቅ አዋጅ ሲሆን፤ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) የረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ በነባሩ ሕግ በአፈፃፀም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች የሚቀርፍ፣ ግልፅና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የኢትዮጵያ ሕንፃዎች አዋጅን፤ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል፡፡
በተመሳሳይም የተከበሩ እሸቱ ተመስገን
(ዶ/ር) የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
የሪል እስቴት ልማቱ አቅርቦት እጅግ ወደኋላ የቀረና የህዝቡን ፍላጎት የማያሟላ በመሆኑ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ እና በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግስትን ጥቅም የሚያሳጣ እንዳይሆን ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል፡፡
በመቀጠልም ምክር ቤቱ በውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ማሻሻያ አዋጅ ለማፅደቅ የቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አዳምጧል፡፡
የተከበሩ ዶ/ር ዲማ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ ኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ለመተግበር የሚያስፈልጉ ደንብና መመሪያዎችን አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውክልና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እና ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አለመስጠቱ አዋጅ ቁጥር 1072/2ዐ10 ተፈፃሚ ለማድረግ ተቋሙ መቸገሩንና የተቋሙ ሥራ መጓተቱን ቋሚ ኮሚቴው ተገንዝቧል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ አዋጁን ከመረመረ በኋላ አስፈላጊነቱን በሙሉ ድምፅ የተቀበለው መሆኑን ጠቁመው፤ የተከበረው ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን እንዲያፀድቀው ጠይቀዋል፡፡
ምክር ቤቱም በቀረበው የረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ማሻሻያ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1358/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል፡፡
(ፖርላማ)