በግንባታ ስራ ላይ ለተሰማሩ ተቋራጮችና አማካሪዎች የተዘጋጀው የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የተዘጋጀውና ትኩረቱን Construction Material Management እና Construction Human Resource Management ላይ ያደረገው የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በቢሮው በተከታታይነት እየተሰጡ ከሚገኙና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዓቅም ከሚያጎለብቱ ስልጠናዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በዚሀ ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 250 ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በቀጣይም በሁለተኛ ዙር Construction Claim and Dispute Resolution በሚል የስልጠና ርዕስ ላይ ስልጠናው አንደሚቀጥል ከቢሮው የዓቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ቢሮው በርካታ ግንባዎችን በጥራት በማከናወን ለአገልግሎት እያዋለ ከመሆኑ ጎንለጎን የኢንዱስትሪውን ተዋንያን ዓቅም የሚያጎለብቱ ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት የከተማው ኮንስትራክሽን ዕድገት ላይ የላቀ የድርሻ እያበረከተ ይገኛል።
(አአዲግቢ)