✅"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?"
🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው።
💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል።
⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል። የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ ውኃ መጠጣት አለበት።
🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል።
🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል።
⚡️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው።
https://t.me/ethioengineers1