✅ጨረታ ውድቅ ሊሆንባቸው የሚችሉ ምክንያቶች
⚡️ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም የወጣው የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 66 "የፌደራል መንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ (PPPAA - Federal Public Procurement and Property Administration Proclamation) ቁጥር 1333/2016 ስለግዢ የተደነገገ ሕግ ነው።
⏺በዚህ ህግ አንቀጽ 26 ላይ "ጨረታን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ ስለማድረግ" የፈቀደ ሲሆን ይህንን ለማድረግ ያስቀመጣቸው ምክንያቶች፦
~ በግዢ አፈጻጸም ውጤት የሚያዛባ ስህተት ካገኘ
~ የተሻለ የሥራ ወይም ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ጥቅም ካገኘ
~ የቀረቡት ተጫራቾች የጨረታውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ከሆነ
~ የቀረበው ዋጋ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ካጠናው የገበያ ዋጋ ከፍተኛ ልዩነት ካለው
~ በጨረታው ያሸነፈው አካል ያስገባው ዋጋ ለጨረታው ከተያዘለት በጀት በላይ ከሆነ
~ ተጫራቾች የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት እንደተመሳጠሩ የሚያሳይ መረጃ ካለ
በእነዚህ ምክንያት ጨረታ ያወጣው አካል ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ሊሰርዝ ይችላል ነገር ግን በዚህ ህግ መሰረት ጨረታው ከተሰረዘ ምክንያቱን የሚገልጽ ማስታወቂያ ለተወዳዳሪዎች ማሳወቅ ይኖርባቸዋል በተለይ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በዚህ መሰረት ጨረታን ውድቅ ቢያደርጉ ተጠያቂ አይሆኑም።
https://t.me/ethioengineers1