✅በጋራ የኮንስትራክሽን ሥራ ንግድ ፍቃድ ስታወጡ ስለስያሜው {ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት}
በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ አክሲዮን ማኅበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሽርክና የሚባሉ ከአንድ በላይ የሆኑ አባላት በጋራ ሆነ ንግድ ፍቃድ የሚያወጡባቸው ዘርፎች አሉ እነዚህ ስያሜዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በዚህ ክፍል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር—ኃ.የተ.የግ.ማ (Private Limitted Company - PLC) እና የአክሲዮን ማህበር - አ.ማ (Social Company - SC) ያላቸውን አንድነትና ልዩነት እንመለከታለን። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።
ተመሳሳይነታቸዉ:-
• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣
ልዩነታቸዉ:-
አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም።
〰️ አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም
〰️ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
〰️ አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።
https://t.me/ethioengineers1