በጌታው እጅግ የተገፋው አገልጋይ ወደ ጫካ ይሸሻል። በጫካ ውስጥ እያለም በመዳፉ ውስጥ እሾህ የገባበት እና በዚህም ምክንያት በህመም ላይ አንበሳ ያጋጥመዋል።
አገልጋዩ ሳይፈራ በድፍረት ወደ ፊት በመሄድ እሾህን በእርጋታ ያወጣለታል እፎይታ ያገኘው አንበሳም ምንም ሳይጎዳው ይሄዳል። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ የ'ባሪያው' ጌታ ወደ ጫካው አደን መጥቶ ብዙ እንስሳትን ያድንንና ይይዛል እናም በአንድ 'ኬጅ' ውስጥ ያኖራቸዋል።
ይሄኔ የጌታው ጠብደል አዳኞች ጫካው ውስጥ አገልጋዩን ይይዙትና ጌታው ፊት ለፍርድ ያቀርቡታል። ጌታውም አስቀድሞም አይወደዉም አሁን ይባስ ብሎ ከቤት ጠፍቶ ስለነበር ወደ ታደኑት አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል ወሰነበት እና ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ።
በዚህ ጊዜ የሚመጣበትን መከራ ያወቀው አገልጋይ በአበሳው ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ቶሎ እንዲሞት እየጸለየ ነበር፤ የወረወሩት ሰዎችም ከምኔው በልተው ይጨርሱታል ብለው እየጓጉ ነበር።
በአንበሳው ጉድጓድ ረብሻ ተነሳ፤ አንበሶች እርስ በራስ ተናከሱ... ሌሎች አንበሶች ሊበሉት ሲራወጡ አንድ አንበሳ ይከላከልለት ነበር። ሌሎቹን አናብስት በኃይሉ ጸጥ ያሰኘው አንበሳው አገልጋዩን በፍቅር ይልሰው ጀመር፤ ለካ በመዳፉ እሾህ ገብቶ ሳለ እሾሁን የነቀለለት አገልጋዩ መሆኑን አልዘነጋም ነበር። አንበሳው ውለታ አልረሳም።
***
ሞራል - እንደ ሰው የተቸገሩትን መርዳት አለበን፤ እርዳታ የተቀበልን ደግሞ ውለታ መዘንጋት የለብንም።
ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል
@ethio_tefer0 @ethio_tefer0
🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽
https://t.me/ethio_tefer