የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 1ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 248877 ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ . ም በዋለው ችሎት የወራሽነት ማስረጃ የወሰደ ሰው በሕግ በታወቀ ጋብቻ ውስጥ ወይም እንደ ባልና ሚስት ግንኙነት ወይም ከሁለቱ በአንዱ በሕግ በሚታወቅ ግንኙነት ውስጥ እንዳልተወለደ ከተረጋገጠ የሟች ልጅ እንደሆነ በመግለጽ ከአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ነው ተብሎ የተሰጠ ማስረጃ ጸንቶ ሊቀጥል የሚችለው ሟች ልጄ ነው በማለት የተቀበሉት ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 131 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት እና በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 143 እና ተከታዮቹ መሠረት አባትነት በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚታወቅባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን በመግለጽ በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ሲቀርብ መሆኑን: ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ የሚወስዱት መብት ለማቋቋም በማሰብ እንደመሆኑ ይህን ማስረጃ በመጠቀም በሚደረግ ተግባራት የሶስተኛ ወገኖች መብቶች ሊነካ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከግምት በማስገባት ማስረጃውን የሚሰጠው ፍርድ ቤትም የወራሽነት ማስረጃ ሲሰጥ ጠያቂዎቹ ከሟች ጋር አለን የሚሉትን ግንኙነት በተገቢው ማስረጃ እንዲያረጋግጡ ማድረግ እንደሚኖርበት: በዚሕ አግባብ ተረጋግጦ የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መሆኑን ማስረጃው የተሰጠው ሰው ባላስረዳበት ሁኔታ ማስረጃውን በመቃወም ክስ ያቀረበ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው የመካድ ክስ እንዲያቀርብም ሊፈቀድለት አይገባም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
JOIN ስለ-ህግ ABOUT-LAW
Telegram- https://telegram.me/ethiolawblog
Facebook- https://m.facebook.com/aboutlawlegalservice
LinkedIn- https://www.linkedin.com/company/aboutethiopian-law
TikTok- https://www.tiktok.com/@aboutethiopianlaw1?_t=8qe3Ip7153m&_r=1