የሲቪል ማኅበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል”፣ “ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ” እና "የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች" የተባሉ ሲቪክ ድርጅቶችን ማገዱን ዋዜማ ሰምታለች። ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማናቸውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል። ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት፣ ድርጅቶቹ ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆነው መሥራት ሲገባቸው ከዓላማቸው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የሕዝብ ጥቅምን በሚጎዱ ተግባራት ላይ ተሠማርተዋል የሚል ነው። የድርጅቶቹ የባንክ ሒሳብም ታግዷል ተብሏል። እገዳው መንግሥት በሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ ምንጮችም፣ እገዳው የተላለፈበት ሂደት ግልጽ እንዳልኾነላቸው ተናግረዋል።
📻Wazema Radio
JOIN ስለ-ህግ ABOUT-LAW
Telegram- https://telegram.me/ethiolawblog
Facebook- https://m.facebook.com/aboutlawlegalservice
LinkedIn- https://www.linkedin.com/company/aboutethiopian-law
TikTok- https://www.tiktok.com/@aboutethiopianlaw1?_t=8qe3Ip7153m&_r=1
📻Wazema Radio