የሰበር ችሎት በ ሰ/መ/ቁ. 213123 በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም፡
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 መሰረት ተከራካሪዎች ካቀረቧቸው ማስረጃዎች በተጨማሪ ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ የማስቀረብ ስልጣን እና ኃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡ ሕጉ ኮመን ሎው (common law) እና ኮንቲኔንታል ሎው (continental law) የሕግ ሥርዓት የሚከተሉ ሀገሮችን አጣምሮ የያዘ እና ከኮመን ሎው የህግ ሥርዓት ከሚከተሉ ሀገሮች በተለየ ለዳኛው ጉዳዩንና ግራቀኙ የሚያቀርቡትን ማስረጃ ከማዳመጥ ያለፈ ተግባር እንደሰጠው ያሳያል፡፡ ድንጋጌው እውነትን የመፈለግ ዓላማ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንዳለው የሚያሳይ እና ዓላማው እንዲሳካ የማድረግም ኃላፊነት የዳኛውም እንደሆነ ያስረዳል፡፡
በመዝገቡ ላይ ሰራተኛው ከመስሪያ ቤቱ የወሰደው ብድር ስለመከፈሉ ሰራተኛው የስራ ውሉ ሲቋረጥ የተሰጠውንና ዕዳ እንደሌለበት የሚገልጸውን ክሊራንስ አቅርቧል። በዚሁ መሰረት የስር ፍርድ ቤት ሰነዱን በማስረጃነት አጣቅሶ ከዕዳ ነጻ አድርጎታል።
በአሰሪው በኩል የቀረበው መከራከሪያ ክሊራንስ ቢሰጠውም ዕዳው ከደመወዙ ሲቀነስ አልነበረም የሚል ነው።
ችሎቱ ከላይ በሁለቱ የህግ ስርዓቶች የዳኛውን ሚና በንጽጽር ከለየ በኋላ በደረሰበት ድምዳሜ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሲሽር በሐተታው ላይ እንዳሰፈረው፥
የሥር ፍርድ ቤቶች ዕዳው ስለመከፈል አለመከፈሉ የ1ኛ ተጠሪ የደመወዝ መቀበያ ፔሮል በማስቀረብ ጉዳዩ በተገቢው ማስረጃ ተረጋግጦ እንዲወሰን ማድረግ ሲገባቸው ይህን ሳያጣሩ ክሱን ውደቅ ማድረጋቸው በሕግ የተጣለባቸውን ክርክርን የመምራት ኃላፊነት ያልተወጡ ስለመሆኑ ስለሚያረጋግጥ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ምን ትላላቹ?
በኔ በኩል ምንም እንኳን የኮንቲኔንታል ሎው (continental law) የህግ ስርዓት የዳኛው ሚና ከሙግት ታዛቢ ይልቅ መርማሪነቱ ቢጎላም ተከራካሪው በእጁ ያለውን ማስረጃ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል ማለት አይደለም። እንዲያ ካደረገ ሚናው ከዳኝነት ይልቅ ወደ አንደኛው ተከራካሪ ጠበቃነት ያዘነብላል። ( Abraham Y.)
Credit to Abraham Y. ( @ethiopianlegalbrief )