የሚኒስሮቹ አሿሿም የህጋዊነት ጥያቄ አስነሳ!
በትላንትናው ዕለት ማለትም ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሦስት ሚኒስትሮችን መሾማቸው ዋነኛ ዜና ሆኖ ውሏል። ከዛም ባሻገር ህጋዊነቱ ላይ ጥያቄ ተነስቶበታል፣ በመሆኑም ጉዳዩ አከራካሪ ሆኗል። ይህን ሁኔታ ተከትሎም የህግ ምሁራን የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሙያዊ አስተያየትና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም ምክንያት በርካታ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል፣ ከእነዚህም መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችን በቀጥታ መሾም ይችላልን? በአንድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ ባልና ሚስትን መሾምስ የጥቅም ግጭት/Conflict of Interest አያስከትልምን? በሀገሪቱ ብቃት ያለው ሰው ጠፍቶ ነው ወይ የአንድ ቤተሰብ አባላትን በካቢኔያቸው ውስጥ ለመሾም የተገደዱት? ወዘተ. የሚሉት ይገኙበታል።
እኔም የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች መሠረት በማድረግ እንደ አንድ የህግ ባለሞያ ሀሳቤን እንደሚከተለው ለመግለጽ ወደድሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችን በዕጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያጸድቃል እንጂ በቀጥታ የመሾም ስልጣን የላቸውም። አይደለምና የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል የሚሆኑ ሚኒስትሮችን ቀርቶ የሚኒስትሮች ም/ቤት አባል የማይሆኑ ኮምሽነሮችን መሾም አይችልም።
ለምን የተባለ እንደሆነ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 74(2) ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ም/ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለስራው ብቃት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያስጸድቃል በማለት ይደንግጋል እንጂ ሚኒስሮችን ራሱ እንዲሾም ስልጣን አልሰጠም።
ህገ መንግስቱ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በአንቀጽ 55(13) ላይ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግስት ፍርድ ቤት ዳኞችን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን፣ የኮምሽነሮችን፣ የዋና ኦዲተርን እንዲሁም የሌሎች ሹመታቸው በምክር ቤት መጽደቅ ያለበትን ባለስልጣኖች ሹመት ያጸድቃል ስለሚል ከእነዚህ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች አንጻር ካየነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ሹመት ህጋዊ መሆኑ ላይ ጥያቄ ያስነሳል።
በሌላ በኩል በአገሪቱ ያን ያህል ሰው የጠፋ ይመስል የተወሰኑ ሰዎችን ከአንዱ መስሪያ ቤት ወደ ሌላኛው መስሪያ ቤት እያዘዋወሩ መሾሙስ ተገቢ ነውን ለሚለው ጥያቄም መልሴ በፍጹም አይደለም የሚል ይሆናል። በተለይም የአንድ ቤተሰብ አባላት በአንድ ካቢኔ ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወስኑ ማድረግ የጥቅም ግጭት የሚያስከትል መሆኑ አይቀርም።
ከሁሉም በላይ ግን ባል ሚኒስትር ሆኖ የሰራበትን መስሪያ ቤት ሚስት ሚኒስትር ሆና ስትሄድ በመ/ቤቱ ሰራተኛ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ጫና እና ምናልባትም የቀድሞው ሚኒስትር በስራ ሒደት የፈጠረው ችግር ቢኖር ወይም ያለአግባብ ያስከፋቸው የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ቢኖሩ አዲሷ ሚኒስትር የእሳቸውን ገበና በድፍረት በማጋለጥ የማስተካከል ዕድላቸው ጠባብ ነው የሚሆነው።
ለማንኛውም የሚኒስትር መስሪያ ቤቶቹ ሠራተኞች በየመስሪያ ቤቶቹ የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ የተሰማቸውን 'ደስታ' የገለጹ ሲሆን በእነሱ አተያይ ሹመታቸውም ያለቀለት ይመስላል። ለመሆኑ የሚኒስትሮቹ ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ሲቀርብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቢቀርስ ውጤቱ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? እስቲ ተወያዩበት!
sisay m. Addisu