#DNA(የዘረ-መል ምርመራ) ለአባትነት ክስ አቅራቢ ማስረጃ አይሆንም።🤔
አባትነት ክስ በፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚችለው በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 143(ከሀ -ሠ) ባሉ አምስት ምክንያት ብቻ ሲሆን አባትነት ክስ አቅራቢ የዘረ መል ምርመራን(DNA) ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የማይችል ሲሆን ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የሚችለው ክስ የቀረበበት ወገን በመካድ አቤቱታ በተሻሻለው ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 167 ነው። በተሻሻለው ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 143 ከተዘረዘረው የአባትነት ክስ ምክንያት ወይም ማስረጃ ሊሆኑ ከሚችሉት ውስጥ የዘረ መል ምርመራ(DNA) በማስረጃነት አላሰፈረውም። ይህንን ሀሳብ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 145 የሚያስረው ሲሆን በአንቀጽ 143 ከተገለጹት ማስረጃ ውጪ አባትነት ክስ በፍርድ ቤት ሊረጋገጥ እንደማይችል ያስቀምጣል።