በሞተ ሰው ስም ቀደም ብሎ የተሰጠን ውክልና በመያዝ የሚቀርብ ክስ ፣ የሚደረግ ክርክር እና የሚሰጥ ውሣኔ እንዳልቀረበ እና ውሣኔም እንዳልተሰጠ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2232(1) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 57 ዴንጋጌዎች መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅፅ 17 ላይ በሰ/መ/ቁ 95587 ጥቅምት 28/2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቶታል።