ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀል ከሚፈፅሙ ግለሰቦች ተጠንቀቁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡
ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታዉቋል።
“በአዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ስልኮች እየተደወለ እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል ፣ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው ፣ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን ነው” በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች የማጭበርበር ወንጀል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ የምርመራ መዛግብቶችን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው አንዳንዶቹ የማጭበርበሪያ ስልቶች ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲኤምም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል።
ፖሊስ አያይዞ እንደጠቀሰው ወንጀሉን ለመከላከል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የተለያዩ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ቢተላለፉም አሁንም ወንጀሉ እየተፈፀመ ሲሆን ግለሰቦች የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው እና ጥሪው እንደደረሳቸው ወደ ተግባር ከመግባታው በፊት አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ባንክ በመሔድ እውነታውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
ፖሊስ መሰል ወንጀሎችን ለመቆጣጠር ከሚሰራው ሥራ ባሻገር አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ መረጃውን ለፀጥታ አካላት በመስጠት ህብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።
‼️Join & Share
📢 ::@samitech0
👥 ፡@Samitech0