የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ እቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Air Cargo Pharma Service of the Year, Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Cargo Airline of the Year, Africa) በመባል ሁለት ሽልማቶች ከ “Aviation Achievement Awards” (AAA) የተበረከተለት መሆኑን ሲገልጽ በደስታ ነው።
እነዚህ ሽልማቶች አየር መንገዳችን ለልህቀት፣ ፈጠራ እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ሲሆን አየር መንገዳችን ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ተከትሎ በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችለዋል።
አሸናፊዎች እንድንሆን ላበቁን የምንጊዜም አጋሮቻችን እና ታታሪ ሰራተኞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎ