🙏እናመሰግናለን ወልዴ👉የባለፈው ክረምት የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡና በርካታ ተጫዋቾች ጥለውት ሄደዋል አንዳንዶች ኢትዮጵያ ቡና ቤት ያደጉ በማይመስል መንገድ ለድርድር እንኳን ስልካቸው ዘግተው ሌላ ክለብ ሲፈርሙ አይተናል ፤
....አንዳንዶች አልተደራደርንም ላለማለት ክለቡን የሚገዛ ብር ጠርተው ጥለውን ሄደዋል ፤ ህመማቸውን አስታመን፤ ጉዳታቸውን አመት ሙሉ ተሸክመን በነፃ ደሞዝ ስንከፍላቸው የነበሩ ተጫዋቾች እንኳን በትንሽ ብር ልዩነት ጥለውን ሲሄዱ ያለአገልግሎት የበላንበትን ጊዜ እንኳን እንካስ አላሉም ፤ ከባድ የጉልበት ቀዶ ጥገና እንደሚስፈልገው የህክምና ቡድኑ እየተናገረ ይሁን ግድ የለም ሁሉንም ከምንለቅ እሱ እንኳ ይቅር የተባለው ተጫዋች እንኳን የህክምና ጉዳቱን የማያውቅ ክለብ ደህና ብር ይከፍለኛል ብሎ ሲሄድ የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጨዋቾች ውስጥ ውለታ ምንም ያህል ቦታ እንደሌለው ማሳያ ነው ።
👉በዚህ ሁሉ መሃል በዚህ ሁኔታ ውስጥ ክለቡን ትቼ አልሄድም በማለት በድርድር ግዜ ክክለቡ ጋር የነበረውን ልዩነት በማጥበበ ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ዉሉን ያራዘመ ብቻኛ ተጫዋች ነው ።በአሁን ሰዓት የክለቡ ጠንካራ ክፍል የሆነውን የተከላካይ ክፍልን ደጀን በመሆን ያለውን ሁሉ በመስጠት እያገለገልን ያለው ወልደአማኑኤል ጌቱ ነው ።ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን።
እናመሰግናለን በርታልን ወልዴ 👆❤️
@Ethiopian_Coffee_Sc@Ethiopian_Coffee_Sc