ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


✅ በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

➡️ ጌታችን ለምን ተጠመቀ ?

1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ ማቴ. 3፥16

2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ ማቴ 11፥29 ለትምህርት ለአርአያ ዮሐ. 13፥1-17

4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

➡️ ጌታችን መች ተጠመቀ ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ ሉቃ. 3፥23

➡️ ጌታችን ስለምን (በ30) ዓመት ተጠመቀ?

በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ.  3፥6-10 ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ይህ ልጄ ነው ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ ማቴ. 3፥16

➡️ ጌታችን በዮሐንስ እጅ ለምን ተጠመቀ ?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ  ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡



➡️ ጌታችን ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው?

በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

➡️ ጌታችን ለምን በውሃ ተጠመቀ?

እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)

➡️ ጌታችን ለምን በሌሊት ተጠመቀ?

በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ.9፥2

አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡


❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

             ጥር ፲፪ (12) ቀን

በዓለ ቅዱስ ሚካኤል
/ቃና ዘገሊላ/


❤ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በሠርግ ቤት ተገኝቶ የመጀመርያውን ተአምር ላደረገበት መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል እስራኤል ወደ ተባለ ቅዱስ ያዕቆብ ለተላከበት ከወንድሙ ከኤሳው ፈርቶ ሳለ ላዳነበት ለወራዊ በዓሉ፣ ለታላቁ ሰማዕት ለምሥራቅ ሰው ጽኑዕ ኃይለኛ ለሆነ ለቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍት በዓልና ለቅዱስ ይስሐቅም ልጅ ለቅዱስ ያዕቆብ ለልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

2k 0 15 8 86

Forward from: ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
የአቤል መክብብ አዲስ የመዝሙር አልበም - ተመስገን

https://youtube.com/playlist?list=PLSoiqK1UfWp8mr2enSQfrrKbhLo0uxq42&si=w3WHpVIzy_I_DxIR


ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።
እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።
ገላትያ 3፥27_29


በዓለም ዙሪያ የምትገኙ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛችሁ ሁሉ

እንኳን አደረሳችሁ!


የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ፣ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ታቦቱን ተከተሉ፤ ኢያሱ 3:3






መልካም የጥምቀት በዓል 💗
🌺💚🌺💚🌺💚🌺💚🌺

3k 0 16 6 63

"በተመሳሳይ ኃጢያት በተደጋጋሚ ብትወድቁም በወደቃችሁበት ቦታ ሳትቆዩ ወደ እግዚአብሔር ሩጡ። አብዛኛዎቹ የቀደሙት ኃጢያቶች በእኛ ላይ የሚበረቱት ልምድ ሆነዉብን ስለኖሩ ነው። እንደዚህ ያሉት ኃጢያቶችም ከጊዜና ከፅኑ ፍላጎት ጋር ብቻ ነው ድል የሚነሱት።"

(ቅዱስ ኔክታርዮስ)


#ጾመ_ገሃድ(#ጋድ)


ጥር አስር በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሳይቀመሱ ምዕመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ።


በዚች ዕለት ምዕመናን እስከ ምሽት እንዲጾሙት ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዐርብ ቀን ቢብት በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጠዋት በመብላት ምዕመናን ሁሉ በዓሉን እንዲያከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓሎቹ ናቸውና።

እኛ በዚህ በኃላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል ዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን

የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዐርብ በሚብትበት ጊዜ በሁለቱ ዕለታት ፈንታ ሌሎች ተለዋጭ ዕለታትን እንድንጾማቸው ይገባል በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብጻውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።

በይረሙን( በዓለ አስተርዕዮ ወይም ከተራ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን(ቅዳሜ) ቢብት ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽቱ ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።


በጥምቀትም ዕለት ከእኩለ ሌሊት በፊት ተነስተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቁርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።

የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያም ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዓሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም።


እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲያከብሩ አዘዋል ይኸውም መድኀኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።

መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዐርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና።


እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮረዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

መጽሐፈ ስንክሳር


#ማስታወሻ


#አልሰማንም_አላየንም_እንዳትሉ_ነገ_እስከ_ምሽቱ_12_ሰዓት_ነው_የሚጾመዉ።

#ቅዳሜ_ከጥሉላት_ምግብ_ብቻ_ነው_የምንቆጠበዉ_እንጂ_ከመብል_አንከለከልም

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!


"አቤቱ አንተን ደስ ከማያሰኝ ሐሳብ እንለይ ዘንድ መለየቱን ስጠን....አቤቱ የእውቀት ዓይኖችን ስጠን፤ ዘውትር አንተን ያዩ ዘንድ ፤ጆሮቻችንም ያንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ።"

ቅዳሴ እግዚእ

3.9k 0 26 4 128

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡
የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።እግዚአብሔርም አለ።‹‹ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።››እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ከተማይቱንም መሥራት ተው።ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ።እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። (ዘፍ.፲፩፥፩-፱)
አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹ኑ እንውረድ›› ባሉት መሠረት ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሦስት መሆናቸው እንረዳለን፤ የስም ሦስትነታቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ የግብር ሦስትነታቸውስ ደግሞ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ የመሆኑ ምሥጢር ነው፤ የአካል ሦስትነታቸው ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ስላላቸው ነው፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመሆኑ የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን? የሚል ጥይቄ የተነሣ እንደሆነ መልሱ‹‹አዎ፤ እንደ ሰው ነው›› ይሆናል፤ ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው፤ የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ በሰማይና በምድር፣ በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ሕያው ባሕርይ ነው፡፡‹‹ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው››እንዲል፤ (ኢሳ.፹፮፥፩-፪) የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ ወዘተ በመሳሰሉት ነው።
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!

5k 0 28 2 103

እንኳን ለአባታችን እና ለአምላካችን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ


ነገ ጥር 7 አጋእዝተ ዓለም ፈጣሪያችን ቅድስት ሥላሴ ናቸው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውሩን🙏

5k 0 26 36 215

አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።

ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።


(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)

4.9k 0 35 3 109



🕯"ከሞትክ በኋላ ሰዎች በምን ያህል ፍጥነት እንደሚረሱህ ብታውቅ ኖሮ፡ በሕይወትህ ውስጥ ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም ለማስደሰት አትፈልግም ነበር።"🕯


»  ቅዱስ ዮሐንስ ፈወርቅ

5.6k 0 31 5 142

"ሰው ሆይ! ጻድቅ መሆንን ትወዳለህን? አዎን ትለኝ እንደሆነ፥ እንግዲያውስ ለራስህ ንፉግ ለሌላው ግን ቸር ሁን፡፡"


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌺 🌺 🌺

6.7k 0 19 24 162

🎂🍰🧁❤️

እንኳን ተወለድክ መምህር!

አመለ ሸጋው በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው መምህር ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ልደት ነው::እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን

"ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ"

ከላይ የምታነቡት መምህር ዲያቆን ሔኖክ ትምህርት ከሰጠ ቡኃላ የሚጠቀማት ፅሁፍ ናት። መምህራችን የአገልግሎት ዘመንህ በቤቱ ይለቅ 🤲 ነበሩ ፣ ጠፉ ፣ ተበተኑ ከመባል ይሰውረን ።

እንኳን ተወለድክ ትሁቱ መምህር Henok Haile 🥰

መልካም ልደት

🎂 🍰 🧁 ❤️

6.5k 0 11 41 385

አንዳንድ ጊዜ ይደክማል ሁሉም ነገር ያስጠላል አለም ትሰለቻለች መፈጠራችንንም ልንጠላ እንችላለን በዚህ ሁሉ ስቃይና ግርግር መሃል ግን ዝቅ ብሎ የሚያነሳን እርሱ እግዚአብሔር አለ ሺህ ጊዜ ብናጠፋ ሺህ ጊዜ ይምረናል እርሱ እግዚአብሔር መልካም ነው የህይወታችንም መሰረት ነው🙏

6.6k 0 32 9 221

ሰውን ከማስተካከል ራስን ማስተካከል ይቀድማል‼❤😍🙏

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ።

ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ። ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ። ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት። ይህን ወዷልና፤ (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ 66፥17)።

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ።

7.1k 0 35 2 109

ሉቃስ 2

¹ በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።
² ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ።
³ ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ።
⁴-⁵ ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
⁶ በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥
⁷ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
⁸ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
⁹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
¹² ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
¹³ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦
¹⁴ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
¹⁵ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
¹⁶ ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።
¹⁷ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ።
¹⁸ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሩአቸው ነገር አደነቁ፤
¹⁹ ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።

20 last posts shown.