በምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
ታህሳስ 10/2017 ጅማ፡- በጅማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የባለድርሻ አካላት የምግብና የጤና ግብዓቶች ቁጥጥር የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ጤናው ሴክተር ላይ ብዙ ሪፎርም መሰራቱን ገልፀው የጤና ፖሊሲያችን ትኩረቱ እንደቀድሞው መከላከል ላይ ብቻ ሳይሆን አክሞ ማዳንን እንደሚጨምር አስታውቀው በአካባቢው የሚገኙ የጉምሩክ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ሌሎች ተቆጣጣሪዎች ሀገርና ህዝብን ከህገወጥ ምግብና የጤና ግብዓት ለመከላከል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አድንቀው ህገወጥ የጤና ግብዓቶች የጤና ብቻ ሳይሆን የሀገር ደህንነት አደጋም ስለሆኑ የጋራ ስራ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንና በዚህም በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት መልክት ያስተላለፉት የጅማ ከተማ የጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ቶሌራ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ህገወጥ ምግብና የጤና ግብዓቶች ዝውውርን ለመከላከል ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከፌዴራል ፖሊሰ ጋር በጋራ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንን መድረክ ማዘጋጀቱ ለቁጥጥር ስራው ትልቅ አቅም ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው በወይይት መድረኩ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የጅማ ዞን ንግድ ቢሮና ጤና ቢሮ እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን ፅሁፎች ቀርበው ውይይቶች የሚካሄዱ ይሆናል።