ህገወጥ የምግብና የጤና ግብዓቶችን ንግድና ዝውውር ለመቆጣጠር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ
11/04/2017 ጅማ:- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በጅማ የጎምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት በመገኘት ከዚህ ቀደም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱና ኮሚሽኑ በጋራ በሰሩት የሰርቬይላንስና የኦፕሬሽን ስራዎች እንዲሁም በጉምሩክ የቁጥጥር ጣቢያዎች በተያዙ ህገወጥ መድኃኒቶችን ለማስወገድ የሚያስችል ውይይት ከጅማ ዞን የጉምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ቶሌራ ጋር አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት ዋና ዳይሬክተሯ እንደተናገሩት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱና ኮሚሽኑ በጋራ በመስራታቸው ብዙ ውጤቶች መገኘታቸውን በመግለፅ ህገወጥ የመድኃኒት ዝውውር የህብረተሰብ ጤናን አደጋ ላይ የሚጥልና የሁሉንም አካላት ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ተናገረው ህገወጥ መድኃኒቶቹን የማስወገድ ስራ በቅርቡ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የጅማ ዞን የጉምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ቶሌራ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ የኮሚሽኑ መጋዘን በመምጣት መድኃኒቶቹ በሚወገዱበት መንገድ ዙሪያ ለመወያየት ወደኮሚሽኑ በመምጣታቸውና ባለስልጣኑ በየጊዜው ለሚያደርገው የባለሙያ ድጋፍና የጋራ ኦፕሬሽኖች ምስጋና አቅርበው ይህ ትብብር ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።