የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ወደ ፊት ለሚወጡ የትምባሆ ማሸጊያ ፓኬት የሕብረተሰብ ጤና ማስጠንቀቂያ ፅሑፍና ባለቀለም ምስልን አገራዊ አድርጎ ለማዘጋጀት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ፡፡
ታህሣሥ 17 /2017 ዓ.ም የተካሄደውን የመግባቢያ ስምምነት በባለስልጣኑ በኩል የሕክምና መሣሪያዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሻርማርኬ ሸሪፍ ሲፈርሙ እንደተናገሩት አዋጅ ቁጥር 1112/11 ጥንካራ የትምባሆ ቁጥጥር አንቀፆች መካተታቸውን ጠቁመው ስለትምባሆ የጤና ጉዳቶች በሲጋራ ፓኬቱ ላይ 70 በመቶ የባለቀለም የጤና ማስጠንቀቂያ በማስቀመጥ ተጠቃሚዎች ማጨስ እንዲያቆሙ የሚያግዝ አንዱ ነው ብለዋል፡፡
እስካሁን የነበሩት የጤና ማስጠንቀቂያዎች ከውጭ የተወሰዱ ስለሆኑ የተፈፃሚነት ደረጃቸው አነስተኛ በመሆናቸው አዲስ ስትራቴጂ መቀየስ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱራዛቅ አህመድ በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱ በትምባሆ ማሸጊያ ፓኮዎች ላይ የሚወጡትን የምስልና የፅሑፍ የጤና ማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ደረጃቸውን የጠበቁና የሕብረተሰብ ግንዛቤ በማሳደግ የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ አስፈላጊውን ጥረት ተቋማቸው እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡
የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ በቀለ በወቅቱ በአስተላለፉት መልዕክት በቀጣይነት የሚወጡ የጤና ማስጠንቀቂያዎች የሚጨሱትን ብቻ ሳይሆን ለማጨስ የሚያቅዱትን ጭምር ቆንጠጥ የሚያደርጉ ሆኖ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡