ለባህል መድኃኒቶች የገበያ ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል ጥናት ሪፖርት ቀረበ
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ ለባህል መድኃኒቶች ግብዓት የሚሆኑ በርካታ እፅዋቶች እንዳሏት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እነዚህን የባህል መድኃኒቶች ጊዜውና ወቅቱ በሚጠብቀው መልኩ በማምረት ለታካሚዎች ለማድረስ ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሰፊ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
የተደረገውን ጥናት ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው መድረክ ላይ አቶ ፈየራ ሌጂሳ ከባለስልጣኑ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ማስተባበሪያ እንደተናገሩት የባህል መድኃኒቶች ለሐገሪቱ የጤና ስርዓት ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና ግንዛቤ በመውሰድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መድኃኒቶቹ ተገቢውን መስፈርት አሟልተው የሚመዘገቡበትን ሁኔታ እያመቻቸ ሲሆን በቅርቡም በይፋ ወደስራ እንደሚገባ ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ያላለሰለሰ አስተዋፆ ለማበርከት ጠንካራ አቋም እንዲወስድ እና ሴክተሩን በጋራ ለህብረተሰቡ ጥቅም ማዋል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የጥናቱን ውጤት ያቀረቡት አቶ ዳዊት ዲቃሶ በበኩላቸው የባህል መድኃኒቶች የባለስልጣን መ/ቤቱን የምዝገባ ስርዓት ተከትለው እንዲመረቱና እንዲመዘገቡ ያስቻለ ጥናት ሲካሄድ መቆየቱን ጠቅሰው ይህ መድረክም ወደተግባር ከመገባቱ በፊት የሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ እንዲወስዱ የተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ከሚመለከታቸው የፌዴራል መ/ቤቶች፣ የባህል ህክምና ማህበር ተወካዮች፣ የክልል ተቆጣጣሪዎች እና የመድሀኒት አምራቾች ጋር በተደረገው ውይይት መሰረት እያንዳንዳቸው ሊያበረክቱ የምችሉትን አስተዋጾ በማቀናጀት የተሻለ የባህል መድኃኒት ለመጠቀም እንዲያስችል ታስቦ የማጠቃለያ ሀሳብ ለተሳታፊዎች ተገልጾ ወይይት ተደርጎበታል።