የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የአቅመ ደካማ ነዋሪ ቤት አድሶ አስረከበ
ታህሣሥ 22/2017 ቀን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመበት ዓላማ በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታን ለማገዝ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲሰራ የከረመው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዚሁ ስራ አንድ አካል የሆነው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝን ቤት በማደስ ለባለቤቱ አስረክቧል
በቤት ርክክቡ ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት ይህ ቤት በ2 ወራት ውስጥ ታድሶ ለነዋሪዋ ወይዘሮ ስንታየሁ ባህሩ ለማስረከብ ባለስልጣኑ ከግርማ ገብረስላሴ ህንፃ ተቋራጭና ከወረዳው ስራ አስፈፃሚ ተቀራርቦ ሲሰራ መክረሙን ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መንግስት በአዋጅ ከሰጠው መንግስታዊ ኃላፊነት ጎን ለጎን ማህበረሰቡን ለመደገፍ በቂርቆስ ወረዳ 02 ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ በጋሞ ጎፋ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች፣ ለመከላከያ ሠራዊት የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው የባለስልጣኑ ሠራተኞችና አመራሮች ከደመወዛቸው ተቆራጭ በማድረግ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው ታድሶ ለመኖሪያነት ምቹ የሆነውን ቤት ለወይዘሮ ስንታየሁ ባህሩ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ አለሙ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በየጊዜው በወረዳው የሚገኙ ነዋሪዎችን ለመደገፍ እየሰራ ያለው ስራ ለሌሎች ተቋማትም ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረው ቤቱ በዚህ ደረጃ ታድሶ ለነዋሪዋ በመሰጠቱ በስራው የተሳተፉትን ሁሉ ያመሰገኑ ሲሆን ቤቱን በተገቢው ጥራት አድሰው ለዚህ ያበቁት ግርማ ገብረስላሴ ህንፃ ተቋራጭን በራሳቸውና በሚመሩት ወረዳ ስም አመስግነዋል፡፡