ህገወጥ ለምግብነት የማይውል ጨው በማምረት ወደ ህብረተሰቡ ሲያሰራጩ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ንማኔ እንደገለጹት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከብሔራዊ ደህንነት፣ ከሲዳማ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከሀዋሳና ከለኩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመሆን በጋራ ባካሄዱት የሰርቬይላንስ ስራ ሸጋ፣ ሺማና ልዩ አዮዳይዝድ ጨው በሚል ህገወጥ የንግድ ስም ለምግብነት መዋል የሌለበተን ጥሬ ጨው አዮዳይዝድ ጨው በማለት በሀዋሳና በለኩ ከተሞች በድብቅ ሲያመርቱ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን የህገወጥ ተግባር በሚከናወንበት ስፍራ በተደረገ ፍተሻ የማምረቻ ቁሳቁሶች ፣ ተመርተው ለማሰራጨት የተዘጋጁ ለምግነት የማይውል ጨውና በተለያየ የንግድ ስም የተዘጋጁ ማሸጊያዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የሲዳማ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦሪሶ ቡላሾ አጥፊዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን የምርቶቹ ናሙና ወደ ለብራቶሪ መላኩ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ባካሄደው የድህረ ገበያ ጥናት በህገወጥ መንገድ ተመርተው ወደ ገበያ ሲሰራጩ የነበሩ 44 ዓይነት ህገወጥ የገበታ ጨው ምርቶች ህብረተሰባችን እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ህገወጥ ጨው አምራቾች ከነማምረቻ ንብረቶቻቸው ለመያዝ በተደረገው ኦፕሬሽን ህብረተሰባችን ላደረገው ትብብር እያመሰገንን መሰል ድርጊቶችን ለመጠቆም በነፃ የስልክ መስመር 8482 አልያም በአቅራቢያዎት ለሚገኝ ተቆጣጣሪ አካል ጥቆማ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡