የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ አዲስ ተቋሙን የተቀላቀሉ ሠራተኞች ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ጠንክረው እንዲሰሩ ተጠየቀ፡፡
መጋቢት 11/2017 ዓ.ም አዳማ ከተማ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከተለያዩ ተቋማት በዝዉዉር ለተቀላቀሉ አዲስ ሠራተኞች ባለስልጣ መስሪያ ቤቱ የሚሠራቸውን የቁጥጥር ስራዎችን የሚያስተዋወቅና ገለፃ የሚሰጥ ስልጠናን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት አዲስ ተቋሙን የተቀላቀሉ ሠራተኞች ራሳቸውን ከጥቅም ግጭት በፀዳና በመልካም ሥነ ምግባር ታንፀው የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ እንዲያሳኩ ጠይቀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት 15 ዓመታት በሕግ ማዕቀፍ፣ በአደረጃጀት ክለሳ እና በጥራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ዙሪያ በበርካታ የለውጥ ሂደቶች ውስጥ ያለፈ መሆኑን ያብራሩት ዋና ዳሬክተሯ እነዚህ የለውጥ አጀንዳዎች እርስ በእርስ ተሳስረው ለመሄድ የሰው ኃይሉን በቅጥርና በአቅም ግንባታ ማጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ለአዲስ ሠራተኞች በተዘጋጀው ተቋሙን የማስተዋወቅ ስልጠና ላይ ከዋናው መስሪያ ቤትና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የመጡ 34 ሰራተኞች እየተሳተፉ ሲሆን በስልጠናው ላይ የተቋሙን መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የፌደራል ሠራተኞች አስተዳደር አዋጅ 1350/2017 ፣ የተቋሙን ሕግና ፖሊሲ፣የተቋሙ ስትራቴጂዎችና ኢንሼቲቮች እንዲሁም ተግባቦት፣ የደንበኞች አያያዝ፣ ስነባህሪና የጥቅም ግጭት የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበው ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡