የገበያ ፈቃድ ባለቤቶች የመድኃኒት ጎጂ ክስተት ግኝትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ሪፖርት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገለፁ
መጋቢት 12/2017፡- የመድኃኒት ጎጂ ክስተት ሲያጋጥም የመድኃኒት ገበያ ፈቃድ ባለቤቶች ሪፖርት ማድረግ በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ከየገበያ ፈቃድ ባለቤቶቹ ለተወከሉ ብቁ የመድኃኒት ጎጂ ባህሪያት ስርዓት ላይ ኃላፊነት ለሚወስዱ ባለሙያዎች በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የህክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አስናቀች አለሙ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ (2) በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመድኃኒት ጎጂ ባህሪያት ክትትል ሥርዓት መመሪያ ከዚህ ቀደም እንዳዘጋጀ ገልፀው ብቁ የመድኃኒት ጎጂ ባህሪያት ስርዓት ላይ ኃላፊነት የሚወስዱ ባለሙያዎች የመድኃኒትን ደህንነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ብቁ የመድኃኒት ጎጂ ባህሪያት ስርዓት ላይ ኃላፊነት የሚወስዱ ባለሙያዎች ስላለባቸው ኃላፊነቶችና ግዴታዎች ፅሁፍ ቀርቦ ሠፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላ በጋራ መግባባት መድረኩ ተጠናቋል፡፡