ከፋብሪካዎች የሚወጡ የምግብ ዘይትና የዱቄት ምርቶች በንጥረ ነገር እንዲበለፅጉ የሚያስገደድ ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ
መጋቢት 18/2017 አዳማ፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የበለፀጉ የምግብ ዘይቶችና የዱቄት ምርቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል መመሪያ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በመመሪያው ላይ ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሠጡበት የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንደተናገሩት ደቂቅ ንጥረ ምግቦች ለሠው ልጆች የሚያስፈልጉ ወሳኝ ንጥረ ምግቦች ሲሆኑ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ለጤናማ የሰውነት እድገት፣ የበሽታ መከላከል አቅምን የሚያጎለብቱና የምግብ መፈጨትን የሚያፋጥኑ ቫይታሚንና ማዕድናትን እንደሚጨምር ገልጸው ይህ መመሪያ ህዝባችን በሚመገባቸው የዱቄትና የምግብ ዘይት ምርቶች አማካኝነት ወሳኝ ንጥረ ምግቦች እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ረቂቅ መመሪያው በባለስልጣኑ የምግብ ምዝገባና ፈቃድ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ አስፋው ቀርቦ ሠፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ባለድርሻ አካላቱ በመመሪያው ላይ ግልፅ ሊደረጉ የሚገባቸው ባሏቸው ጉዳዮች አስተያየታቸውን አቅርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡