ጾመ ነቢያት:-
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሰም ኅዳር ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የስብከተ ገና ጾም መጀመሪያ ነው::
ይህም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተወለደበት በግብጽ የሚኖሩ ያዕቆባውያን ክርስቲያኖች የሠሩት ነው::
በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ባሕልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሥርዓት አላት::
እነዚህም ሰባቱ የጾም ወራት ናቸው::
1ኛ. ዓቢይ ጾም
2ኛ. የሐዋርያት ጾም
3ኛ. የፍልሰታ ጾም
4ኛ. ጾመ ነቢያት
5ኛ. ጾመ ገሀድ
6ኛ. ጾመ ነነዌ
7ኛ. ረቡዕና ዓርብ የተባሉት ናቸው::
እነዚህንም አጽዋማት ሀብተ ወልድና ሥመ ክርስትና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያገኘ ምእመን ዕድሜው ከሰባት ዓመት በላይ የሆነ ክርስቲያን መምህረ ንስሐው በበሽታ ምክንያት ካልከለከላቸው በስተቀር ሰባቱንም አጽዋማት እንዲጾም ሥርዓት ተሠርቶልናል::
ከነዚህ አጽዋማት መካከል ዛሬ የምንጀምረው ጾም በ4ኛ. ደረጃ ላይ ያስቀመጥነውን ነው:: ይህም ጾም:- ጾመ ነቢያት ይባላል::
ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 28 ቀን ያለው ነው:: ይህን ጾም የምንጾመው ነቢያት በየዘመናቸው ስለመሲህ መምጣት በናፍቆት በመጠባበቅ ይጾሙ ይጸልዩ ስለነበር የእነርሱን አርአያ ተከትለን ከዛሬ ከኅዳር 15 ጀምሮ የክርስቶስን ልደት ከማክበራችን ቀደም ብለን ይህን ጾም እንድንጾም በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተሠርቷል:: በዚህም ምክንያት እንጾማለን::
ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል ማለት ነው:: ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመዥውን ነገር መተው ማለት ነው::
ሃይማኖት ባለበት ቦታ ሁሉ ጾም አለ:: ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘላለማዊ ዝምድና አለው:: ይልቁንም በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ አለው::
የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ባፋቸው አይገባም ነበር:: ዘጸ. 34 -:- 28:: በኃጢአት ብዛት የታዘዘው የእግዚአብሔር መዓት የሚመለሰው ቁጣው የሚበርደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር:: ዮና.3-:-5-10::
በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው የሥራ መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው:: ማቴ.4-:-2:: ሉቃ.4-:-2::
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሠረት መጾም አለብን:: የምንጾመውም ከመብል ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን አባቶቻች "ከመብልና ከመጠጥ ብቻ እንጾማለን አትበሉ ከክፉ ነገር ጭምር ራቁ" እንዳሉን መራቅ ይገባናል::
ስለዚህ በረከት ረድሄት የምናገኝበት ከኃጢአት ከበደል የምንርቅበት ጾም ያድርግልን::
ይቅርታው ቸርነቱ በሁላችን ክርስቲያኖች ላይ ይኑር በአገራችን ኢትዮጵጰያ ላይ ሰላም ያምጣልን ለዘላለሙ አሜን::
🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️