አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አንድ የጽዮን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ ነው::
"ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል" እንዳለች እርሷ እመቤታችን በዛሬው ዕለት እስትንፋስ ያለው ፍጥረት ሁሉ ጽዮንን ከበው ያመሰግኗታል::
በእውነት ጽዮን እናታችን ናት፣ እርሷ መመኪያችን ናት፣ እሷን ከብን እናመሰግናታለን፣ ለጽዮን የጸጋ ስግደት እንሰግድላታለን።
አባቶቻችን እንዳስተማሩን ቅዱሳን መጻሕፍት እንደመሰከሩልን ሰው እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ።
ጌታ ከእመቤታችን በስጋ ተወለደ ።
እርሱ እራሱ ልዑል መሰረታት ማለት እግዚአብሔር እመቤታችንን በንፅህና አጸናት በእመቤታችን ያመኑ ሁሉ ደስ ብሏቸው እንዲኖሩ ይናገራቸዋል ።
( መዝ 130÷131--18)
ጽዮን የሚላት በወርቁ እመቤታችንን ነው ይህም ይታወቅ ዘንድ ይህቺ ለዘለአለም ማረፊያዬ ናት ብሎ ለምድራዊቷ ጽዮን (ለምድሪቱ )አለመሆኑን ያረጋግጥልናል ።
ምክንያቱም ሰማይና ምድር ያልፋሉ ብሎ ራሱ ጌታ በማይታበል ቃል ተናግሯል ።
ስለሆነም ምድሪቱ የዘለዓለም ማረፊያ ልትሆነው አትችልም ለእመቤታችን ግን ይስማማል ይህቺ ለዘለአለም ማረፊያዬ ናት ሲል ለዘለአለም ወላዲተ አምላክ ስትባል የምትኖር ስለሆነ ነው።
ከእርሷ የነሳው (የወሰደው )ስጋ ለዘለዓለም መለኮትን ተዋሕዶ የሚኖር ስለሆነ መርጫታለሁና አድሬባታለሁ አለ
( ትቢ ኢሳ 60÷4) ።
የአስጨናቂዎችሽ ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔር ከተማ (ዘጠኝ ወር ከ 5 ቀን ማሕጸኗን አለም አድርጎ ተመስግኖባታል እና ከተማ አለው )የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል ። ሲል ነው
ምስጋና በዛሬው ዕለት ማኅሌቱ ቅኔው ይፈሳል:: ዕንባዎች በተማፅኖ በደስታ ይፈሳሉ::
የፃድቃን እጆች ለምጽዋት ይፈተሉ:: ድሆች ይጠግባሉ የታረዙ ይለብሳሉ::
በዛሬው ዕለት አብያተ ክርስቲያናት በማኅሌት በሠዓታት በእግዚኦታ በኪዳን በቅዳሴ በትምህርተ ወንጌል ደምቀው አድረው ይውላሉ::
አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይ:-
ጸጋን የተመላሽ ሆይ በምን ስም እንጥራሽ?
የመድኃኒት በር ነሽ፤ የብርሃን መስኮት ነሽ፤ የመንግሥት ልጅ ነሽ:: ሰማይ እንበልሽ ይሆን!
✝ልጅሽ የእውነት ፀሐይ ነው፤ ሐዋርያት ኮከቦችሽ ናቸው፤ (እነዚያ) የልጆችሽ መቅረዞች::
የአትክልት ቦታ እንበልሽ ይሆን!
✝ልጅሽ የወይን ተክል ነው፤ ሐዋርያቱ ሐረጎችሽ ናቸው (እነዚያ) የበኵርሽ ቅርንጫፎች::
✝መርከብ እንበልሽ ይሆን! ቀዛፊው ልጅሽ ነው፤ሐዋርያቱ መርከበኞችሽ ናቸው (እነዚያ) የበኵርሽ ምርጦች::
✝የግንብ ቤት እንበልሽ ይሆን ገንቢው ልጅሽ ነው ሐዋርያቱ ቤተሰቦችሽ ናቸው (እነዚያ) የበኵርሽ ምእመናን::
✝መሠዊያ (መንበር) እንበልሽ ይሆን! ልጅሽ ሊቀ ካህናት ነው፤ ሐዋርያት ተላላኪዎችሽ ናቸው::
(እነዚያ) የበኵርሽ ደቀ መዛሙርት::
✝መሶበ ወርቅ እንበልሽ ይሆን! ልጅሽ የሕይወት እንጀራ ነው ሐዋርያቱ አሳላፊዎችሽ ናቸው (እነዚያ) የበኵርሽ ሥጋ የሚሠዉ::
✝ጽዋ እንበልሽ ይሆን! ልጅሽ የመለኮት ወይን ነው
ዠሐዋርያቱ ካህናትሽ ናቸው (እነዚያ) የበኵርሽ ደም የሚቀዱ ይሏታል:: በማድነቅና በተመስጦም!
"የእግዚአብሔር ጥበብ እንዴት ድንቅ ነው የሥራው ኃይል ትልቅ ነው ፍርዱ ሁሉ ትክክል ነው የስሙ ምስጋና የተባረከ ነው በዕብራይስጢ ማሪሃም የተባለውን ይህችን ቅድስት በሁሉት በኩል ድንግል የሆነች ማርያምን የመረጣትና የወደዳት-:- ከፍ ከፍ ያደረጋት ያከበራት ነውና::
እንግዲህ ምን እንላለን! በእውነት ቅድስት ሆይ ለምኝልን ብቻ እንበላት እንጂ:: ለእርሷ ምስጋና ለማቅረብ የጸዳ ልቡናና አንደበት ያላቸው እንደምን ያሉ ናቸው!
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን ለዘላለሙ አሜን።
@ethiopianorthodoxs