የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት መሥሪያ ቦታና ነጻ ህክምና እንዲያገኙ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታና ነጻ ህክምና እንዲያገኙ ለመንግሥት ጥያቄ አቀረበ፡፡
ማህበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ እንደሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሁሉ፣ መምህራንም የበረሃና የውርጭ አበል እንዲከፈላቸውም ጠይቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙባቸው ክልሎች ሁሉ መምህራኑ የአካባቢውን ማህበረሰብ እያገለገሉ ቢሆኑም፣ “ዩኒቨርሲቲዎች የፌደራል ተቋም ናቸው” በሚል የቤት መሥሪያ ቦታ ሳያገኙ ቀርተዋል ብሏል - ማህበሩ፡፡
መምህራኑ በሚያስተምሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙ የጤና ተቋማት እየከፈሉ እንደሚታከሙ የጠቀሰው ማህበሩ፤ ይህም የሥራ ተነሳሽነታቸውን እንደቀነሰው በመግለጽ፣ ከእነ ቤተሰባቸው ነጻ ህክምና እንዲያገኙ ለት/ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L