አሜሪካ አዲሱን የሶሪያ መሪ ለመያዝ መድባ የነበረውን የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ሰረዘች
አሜሪካ የሶርያውን መሪ አህመድ አል-ሻራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ለመያዝ መድባው የነበረውን የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ከከፍተኛ ዲፕሎማቶች እና ከሃያት ታህሪር አል ሻም (ኤችቲኤስ) ተወካዮች ጋር ውይይት ካደረገች በኋላ ነው የሰረዘችው።
ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባርባራ ሌፍ ከሻራ ጋር የተደረገው ውይይት "በጣም ውጤታማ ነበር" ካሉ በኋላ እርሱም "ለመወያየት ዝግጁ" ሆኗል ብለዋል።
የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ዋና ከተማዋ ደማስቆ የደረሰው የኤች ቲ ኤስ ታጣቂዎች የበሽር አል አሳድን መንግሥት ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ካስወገዱ በኋላ ነዉ።
ዋሽንግተን አሁንም አማፂ ቡድኑን በአሸባሪነት እንደ ፈረጀች ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ዲፕሎማቶቹ በአሜሪካ የሚደገፍ "የሽግግር መርሆዎች" ላይ፣ ቀጠናዊ ሁኔታዎች እንዲሁም አይኤስን የመዋጋት አስፈላጊነት ላይ መወያየታቸውን አረጋግጠዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ባለሥልጣናቱ በአሳድ አገዛዝ ዘመን ስለጠፉት አሜሪካውያን ዜጎች፣ በ2012 በደማስቆ የተጠለፈውን ጋዜጠኛ ኦስቲን ቲስ ፣ እና በ2017 የጠፋውን ሳይኮቴራፒስት ማጅድ ካልማዝ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን አስታውቀዋል።
ጉብኝቱ ከአስር ዓመታት ወዲህ በደማስቆ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መደበኛ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ነው።
ይህ ጉብኝት በሶሪያ የአሳድ ከስልጣን መወገድን ተከትሎ የታየ ድንገታዊ ለውጥ ሲሆን፣ አዲስ ስልጣን የሚረከበውን መንግሥት የአረብ አገራት ድጋፍ ተጨምሮበት አሜሪካ እና አውሮፓ ተጽዕኖ ለማሳረፍ የወሰዱት እርምጃ ነው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም