ይሄ ነገር ስንቱን ባለሙያ ስራ አጥ ያደርግ ይሆን ?
ፖላንድ ጋዜጠኞችን በAI የመተካት እንቅስቃሴ ጀምራለች
በፖላንድ የሚገኝ የሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኞቹን በማባረር በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰሩ አቅራቢዎችን ስራ ማስጀመሩ ተሰምቷል።
ሬዲዮ ጣቢያው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰሩት 3 አቅራቢዎች ስለ ባህል፣ ስነ-ጥበብ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ለወጣት አድማጮች ዝግጅቶችን እንዲደርሱ አስቧል።
ጋዜጠኞችን በAI በተፈጠሩ ምናባዊ ገጸ-ባህሪያት መተካት የመጀመሪያ ስርጭቱንም አካሂዷል።
የጣቢያው ኃላፊ ውሳኔው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለመገናኛ ብዙሃን፣ ለሬዲዮ እና ለጋዜጠኝነት የበለጠ እድል ነው ወይስ ስጋት ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በጣቢያው ላይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ እና የፊልም ሃያሲ ማቴያስ ዴምስኪ ይህንን በመቃወም ከ15,000 በላይ የሚሆኑ የተቃውሞ ፊርማዎችን አሰባስቧል።
ጣቢያው በግብር ከፋዮች የሚደገፍ የህዝብ ጣቢያ በመሆኑ ሰዎችን በAI መተካታቸው አስደንጋጭ ነው ተብሏል።
የሬዲዮው ኃላፊ ማርሲን ፑሊት በ AI ምክንያት አንድም ጋዜጠኛ አልተባረም ያሉ ሲሆን ነገር ግን የሬዲዮ ፕሮግራሙ ተድማጭነቱ "ወደ ዜሮ የቀረበ ስለነበር ነው" ይህንን ያደረግነው ሲሉ አስተባብለዋል።
via reporter