በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ ትምህርቶች ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲኖራቸው እየተሠራ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ ትምህርቶች ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው በዋናነት ከሚሠራው የመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪ ተማሪዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ሲወጡ ያላቸው ተፈላጊነት እንዲጨምር የተለያዩ ሥራዎችን ይሠራል።
በመሆኑም በዚህ ዓመት ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው ትምህርቶችን ዓለም ዓቀፍ እውቅና እንዲያገኙ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
እውቅናውን ለማግኘት በአሜሪካ ሀገር የሚገኝ የትምህርት እውቅና የሚሰጥ ተቋም ምዘና ለማካሄድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ የሚሰጠው እውቅናም ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ትምህርት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ዓለም ላይ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የሚገመግም መሆኑን አብራርተዋል።
የኢንጂነሪንግና ሳይንስ ፕሮግራሞች የሚሰጠው ይህ እውቅና እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ......
https://press.et/?p=140975