የወልዲያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኦክስጅን ማምረት ጀመረ
*******
(ኢ ፕ ድ)
ወልዲያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህክምና አገልግሎት የሚውል ኦክስጅን ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።
የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኑ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተመልክቷል።
በሆስፒታሉ የሚታየውን የኦክስጅን ምርት እጥረት ለመፍታት የሚያስችል ኦክስጅን የሙከራ ማምረት የጀመረው ዛሬ መሆኑን በሆስፒታሉ የባዮ ሜዲካል ባለሙያ አቶ ዮሴፍ ምህረቴ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ቀደም ሲል ሆስፒታሉ ለህክምና የሚያስፈልገውን ኦክስጅን ከደሴና የግል ሆስፒታሎች በማስመጣት ሲጠቀም መቆየቱን አስታውሰዋል።
ይህም በተፈለገው መጠንና ጊዜ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ በህክምና አገልግሎት ዘርፉ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ጠቅሰዋል።
ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን በመትከል ዛሬ ማምረት መጀመሩን ጠቅሰው፥ ማሽኑ በቀን እስከ 200 ሲሊንደር የማምረት አቅም አለው ብለዋል።
ኦክስጅኑን አምርቶ መጠቀም መጀመሩ የተሟላ ህክምና ለመስጠት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በሰሜን ወሎና በወልዲያ ከተማ ለሚገኙ ጤና ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቱን እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በወልዲያ ከተማ የቀበሌ 01 ነዋሪ አቶ አለባቸው አዳሙ በሰጡት አስተያየት፤ ከ6 ወር በፊት በተሽከርካሪ አደጋ የተጎዳ ልጃቸው በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ወደ ደሴ "ሪፈር" መባላቸውን አስታውሰዋል።
በዚህም ለአላስፈላጊ ወጪና መጉላላት መዳረጋቸውን አንስተው፥ አሁን ላይ ሆስፒታሉ በራሱ አቅም ኦክስጅን ማምረት መቻሉ የህብረተሰቡን ችግር እንደሚያቃልል ገልጸዋል።
የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኑ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ትብብር እንደተከናወነ ተመልክቷል።
ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓም