ወርቅ ለማውጣት ሲባል ያልተፈቀዱ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢሮው አሳሰበ
***********
(ኢፕድ)
በትግራይ ክልል ወርቅ ለማውጣት ሲባል ያልተፈቀዱና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የክልሉ የመሬትና ማዕድን ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ ግርማይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤በክልሉ የነበረው ጦርነት የማዕድን ዘርፉ ላይ ህገወጥ ተግባር እንዲስፋፋ አድርጓል።
በዚህም ህገወጥ ማዕድን አውጪዎች ወርቅ ለማውጣት ያልተፈቀዱና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ኬሚካሎች ሲጠቀሙ ቆይተዋል።
ይህም በክልሉ ወንዝ፣ የእንስሳት ሃብት እና በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንና እያደረሰ መሆኑን ተናግረው፤ በክልሉ በህገወጥ መንገድ የማዕድን ንግድ ላይ የሚሳተፉ እና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ የማዕድን አውጪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ይህንን ለመፍታት የቁጥጥር መመሪያ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ፍስሃ፤ ከዚያም ተጠያቂነትን የማስፈን እና ህገወጥ ማዕድን አውጪዎችን ለህግ የማቅረብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይ ደግሞ ለማዕድን አውጪዎች የሚሰጠው ፈቃድ ይቆማል ብለዋል።
በማዕድን ዘርፉ ህጋዊ ያልሆኑትን ወደ ህጋዊ ሥርዓት የማስገባት ሥራ እየተሰራ ሲሆን በዚህም በ30 ማህበራት የታቀፉ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል።
ለነዚህም ህጋዊ ፍቃድ፣ የመሥሪያ ቦታና ሌሎች ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል።
ይህ እንቅስቃሴ በክልሉ የማዕድን ሀብት ላይ ሲታይ የነበረውን ህገወጥ ተግባር እንዲቀንስ እና ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ ክምችት እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
በሳሙኤል ወንደሰን